2 ዜና መዋዕል 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እንዲሁም ንጉሡ ዐሥር የመታጠቢያ ሳሕኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበውን ነገር ሁሉ እንዲያጥቡበት አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኩሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ ዐምስቱን በደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎቹ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ ገንዳው ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሰሎሞን ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎችን አሠርቶ፥ አምስቱን በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ጐን የቀሩትን አምስቱን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ሰሜናዊ ጐን አኖራቸው፤ እነዚህ ገንዳዎች ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚታረድ እንስሳ ሥጋ ሁሉ የሚታጠብባቸው ነበሩ፤ በትልቁ ገንዳ ያለው ውሃ ደግሞ ለካህናቱ መታጠቢያ የሚውል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ደግሞም ዐሥር የመታጠቢያ ሰኖችን ሠራ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ባሕሩ ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ደግሞም ዐሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |