2 ዜና መዋዕል 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ያህል ውሃ የሚይዝ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የሁሉም ጀርባቸው ወደ ውስጥ ነበር። የገንዳው ጐኖች ውፍረት ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ሲሆን፥ ክፈፉም እንደ ኩባያ ክፈፍ ሆኖ እንደ አሸንድዬ አበባ ወደ ውጪ የተቀለበሰ ነው፤ በርሜሉ ሥልሳ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ውፍረትዋም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሯም እንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም ማድጋ ትይዝ ነበር ሠርቶም ፈጸማት፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም አንድ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |