2 ዜና መዋዕል 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ ዐሥር፥ እንደ በሬዎች ያሉ ቅርጾች በኩረው ላይ አዞረበት፤ ኩሬውንም በቀለጠ ጊዜ የበሬዎቹም ቅርጾች በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የገንዳው የውጪው ክፈፍ ዙሪያው በሙሉ አንዱ በሌላው ላይ የተነባበረ ሆኖ በሁለት ረድፍ የተሠሩ ጌጦች ነበሩት፤ እነዚህም ጌጦች በሙሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በበሬዎች ቅርጽ የተሠሩ ናቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ አሥር፥ ጕብጕቦች አዞረበት፤ ኵሬውም በቀለጠ ጊዜ ጕብጕቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |