2 ዜና መዋዕል 32:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 የላይኛውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ፣ ውሃውን በቦይ ቍልቍል ወደ ምዕራቡ የዳዊት ከተማ እንዲወርድ ያደረገም ይኸው ሕዝቅያስ ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ተከናወነለት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 በላይ በኩል ያለውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ ውሃውን ወደ ምዕራብ፥ ወደ ዳዊት ከተማ፥ በቦይ እንዲወርድ ያደረገ ራሱ ሕዝቅያስ ነው፤ ይህ ሕዝቅያስ ሊሠራ ባቀደው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። ሕዝቅያስም በሥራው ሁሉ ተከናወነ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ። ምዕራፉን ተመልከት |