Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 31:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በጌታም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፈለውን ወሰነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ንጉሡ ጧትና ማታ እንደዚሁም በየሰንበቱ፣ በየወሩ መባቻውና በተወሰኑ በዓላት፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ከራሱ ንብረት ሰጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዘወትር ጠዋትና ማታ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በእግዚአብሔር ሕግ በተወሰነው በሌሎች በዓላት ለሚቀርብ መሥዋዕት ንጉሥ ሕዝቅያስ የራሱ ንብረት ከሆኑ በጎችና የቀንድ ከብቶች ይሰጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥ​ዋ​ትና በማታ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በበ​ዓ​ላ​ትም ለሚ​ቀ​ር​በው ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ንጉሡ ከገ​ን​ዘቡ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ወሰነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፈለውን ወሰነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 31:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በየበዓላቱ፥ በየመባቻው፥ በየሰንበታቱ፥ በእስራኤል ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን፥ የመጠጡን መሥዋዕት ማቅረብ በመስፍኑ ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ሊያስተሰርይ የኃጢአቱን መሥዋዕትና ስጦታውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቀርባል።


ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም በሬዎች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ።


እንዲህም ያከበሩት የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንደ ቁርባን ስለሚቀርበው መሥዋዕት አንድ ሺህ ወይፈኖችና ሰባት ሺህ በጎች እንዲሁም ሹማምንቱ አንድ ሺህ ወይፈኖችና ዐሥር ሺህ በጎች ለጉባኤው ሰጥተው ስለ ነበረ ነው።


ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አዛዦች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


“በስድስተኛውም ቀን ስምንት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች