2 ዜና መዋዕል 30:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለጌታ የተቀደሱ ለማድረግ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ የፋሲካውን ጠቦት ያርዱላቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ከጉባኤው መካከል አብዛኛዎቹ ራሳቸውን ያልቀደሱ ስለ ነበሩ፣ ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ላላነጹትና ጠቦቶቻቸውን ለእግዚአብሔር መቀደስ ላልቻሉት ሁሉ የፋሲካውን በጎች ማረድ ነበረባቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከሕዝቡ መካከል ብዙዎቹ ራሳቸውን ያላነጹ ስለ ነበሩ ለፋሲካ የሚሆኑትን የበግ ጠቦቶች ለማረድ አልተፈቀደላቸውም ነበር፤ ስለዚህ ሌዋውያን በእነርሱ ምትክ የበግ ጠቦቶቹን በማረድ ለእግዚአብሔር አቀረቡላቸው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በጉባኤውም ያልነጹ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ላላነጹት ሁሉ የፋሲካውን በግ ያርዱላቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ይቀድሱአቸው ዘንድ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ ፋሲካውን ያርዱላቸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |