Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ የጌትንና የየብናን የአዞጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም አገር ከተሞችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በፍልስጥኤማውያን ላይ ዘምቶ የጋትን፣ የየብናንና የአዛጦንን ቅጥሮች አፈረሰ። ከዚያም በአዛጦን አጠገብና በቀሩትም የፍልስጥኤም ግዛቶች ውስጥ ከተሞችን እንደ ገና ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ዖዝያ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ የጋትን፥ የያብኔንና የአሽዶድን ከተማዎች ቅጽሮችን አፈራረሰ፤ በአሽዶድ አጠገብና በቀሩትም የፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወጥ​ቶም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ የጌ​ትን ቅጥር፥ የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ቅጥር፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ በአ​ዛ​ጦ​ንና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ከተ​ሞ​ችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትንና የየብናን የአዞጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም አገር ከተሞችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 26:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።


ጌታም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን የቊጣ መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ።


ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አስገበራቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።


ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።


የጌታ እጅ በአሸዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መቅሠፍት መታቸው።


ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፥ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት።


ነዋሪዎችዋን ከአዛጦን፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?


ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።


አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።


ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥


የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜ እርሱም ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች