2 ዜና መዋዕል 26:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ። ሕዝቡም “ለምጽ አለበት” ብለው የነገሥታቱ በሆነው መቃብር አጠገብ ባለው ቦታ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በምትኩ ነገሠ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለዋልና የነገሥታቱ መቃብር ባልሆነ እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። ምዕራፉን ተመልከት |