2 ዜና መዋዕል 25:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮስያስ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “የሊባኖስ ኩርንችት፦ ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው’ ብሎ ወድ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኩርንችቱን ረገጠ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ ሚስት እንድትሆነው ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት ወደ ሊባኖስ ዛፍ መልእክት ልካ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል ጠየቀችው፤ ነገር ግን አንድ አውሬ በዚያ በኩል ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ሲል ላከ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው” ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም ዱር አውሬዎች መጥተው ኵርንችቱን ረገጡት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአያስ “የሊባኖስ ኵርንችት ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው’ ብሎ ወድ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ። ምዕራፉን ተመልከት |