Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ለመስጠት ስላደረገው ተስፋ፥ ጌታ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም መብራት እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የዳዊትን ሥርወ መንግሥት ሊያጠፋ አልፈለገም፤ ይህም የሆነው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ስለ ነበርና የዳዊት ዘሮችም ዘወትር ሳያቋርጡ የሚነግሡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተስፋ ቃል ሰጥቶት ስለ ነበር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ነገር ግን ከዳ​ዊት ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን፥ ለእ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቹም በዘ​መ​ናት ሁሉ መብ​ራ​ትን ይሰ​ጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ይሰጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ፥ እግዚአብሔር የዳዊትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አልወደደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 21:7
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።


እርሱም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፤ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ ይመራል።”


በአገልጋዩ በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፥


ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”


ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።


አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ በቀባኸውም ላይ በቁጣ ተነሣህ።


የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ ጎቶሊያ እንዳታስገድለው የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት እንዲሁ ሸሸገችው።


እግዚአብሔር ግን ከዘሩ መንግሥትን እንደማያጠፋ ለአገልጋዩ ለዳዊት ተስፋ ሰጥቶት ስለ ነበር ይሁዳን መደምሰስ አልፈለገም።


ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?


የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።


ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ ጌታ አምላኩ ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው።


ኢዮራም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ ውስጥ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝያስ ነገሠ።


ጉባኤውም ሁሉ በጌታ ቤት ውስጥ ከንጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ጌታ ስለ ዳዊት ልጆች እንደ ተናገረ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል።


እንግዲህ አሁን፥ አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ‘አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆችህ በሕጌ እንዲሄዱ መንገዳቸውን ቢጠብቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም’ ብለህ ተስፋ የሰጠኸውን ለባርያህ ለአባቴ ለዳዊት ጠብቅ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች