Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ሥልጣን ይዞ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞቹን በሙሉ ከጥቂት የእስራኤል አለቆች ጋራ በሰይፍ ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኢዮራም መንግሥቱን ካጠናከረ በኋላ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም አንዳንድ የእስራኤል ባለሥልጣኖችን ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኢዮራምም በአባቱ መንግሥት ላይ ተነሥቶ በጸና ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉ ሌሎችንም የእስራኤልን መሳፍንት በሰይፍ ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 21:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ዖፍራ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄደ፤ ሰባውን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የይሩበኣል የመጨራሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለ ነበር አመለጠ።


የአካዝያስም እናት ጎቶሊያ ልጇ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነሥታ የይሁዳን የነገሥታት ዘር ሁሉ አጠፋች።


ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ወረርዋትም፥ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አላስቀሩለትም።


ቃየንም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ፥ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።


ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድን ሲፈጽም የይሁዳን መሳፍንትና አካዝያስን ያገለግሉ የነበሩትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።


በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥


አሁንም ነዪ፥ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።


መንግሥትም በጸናለት ጊዜ ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባርያዎች ገደለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች