2 ዜና መዋዕል 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኛል፥ ስለ ሆነም የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ድንቅ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የምሠራው ቤተ መቅደስ ትልቅና እጅግ ውብ መሆን ስላለበት፣ ብዙ ጠርብ ያዘጋጁልኛልና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ይህ እኔ ልሠራ ያቀድኩት ቤተ መቅደስ ሰፊና እጅግ የተዋበ መሆን ስለሚገባው እኔም ብዙ እንጨት ቈርጠው በማዘጋጀት የአንተን ሰዎች የሚረዱ፥ የእኔን ሰዎች ወደ አንተ ለመላክ ዝግጁ ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ክቡር ይሆናልና ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኝ ዘንድ፥ እነሆ፥ አገልጋዮች ከአገልጋዮችህ ጋር ይወጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ድንቅ ይሆናልና ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኝ ዘንድ፥ እነሆ፥ ባሪያዎቼ ከባሪያዎችህ ጋር ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከት |