2 ዜና መዋዕል 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲሄድ አባበለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ከጥቂት ዓመታት በኋላም አክዓብን ሊጐበኝ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለርሱና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ብዙ በግና በሬ ዐረደ፤ ከዚያም በራሞት ገለዓድ ላይ አደጋ እንዲጥል አግባባው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ከጥቂት ዓመቶች በኋላም ኢዮሣፍጥ አክዓብን ለመጐብኘት ወደ ሰማርያ ከተማ ሄደ፤ አክዓብም ለኢዮሣፍጥና ለአጃቢዎቹ ክብር ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን ዐርዶ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ አክዓብ በገለዓድ በሚገኘው በራሞት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል ይተባበረው ዘንድ ኢዮሣፍጥን አግባባው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ከጥቂት ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችንና በሬዎችን አረደ፤ ወደደውም፤ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ይሄድ ዘንድ አባበለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ይሄድ ዘንድ አባበለው። ምዕራፉን ተመልከት |