Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እናንተ ግን ለሥራችሁ ሽልማት ይሆንላችኋልና በርቱ፥ እጃችሁም አይላላ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እናንተ ግን በርቱ፤ አትታክቱ፤ ለምትሠሩት መልካም ሥራም ዋጋ ታገኛላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እና​ንተ ግን ለሥ​ራ​ችሁ ዋጋ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና በርቱ፤ እጆ​ቻ​ች​ሁም አይ​ላሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እናንተ ግን ለሥራችሁ ብድራት ይሆንላችኋልና በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 15:7
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።


ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።


በምትሄድበት ሁሉ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ነገር ግን ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥ በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


ይህንንም ስታደርጉ ከጌታ የርስትን ሽልማት እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።


ለሠራሽው ሥራ ጌታ ይክፈልሽ፥ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በጌታ ዘንድ ዋጋሽ ፍጹም ይሁን” አላት።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል።


ማንም በዚያ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል፤


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ በርህንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።


ይህም ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ነው። በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።


በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ሽልማት ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤


ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።


በስውር ላለው አባትህ እንጂ በሰዎች ዘንድ ጾመኛ ሆነህ እንዳትታይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።


“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።


ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”


ከወርቅና ከክቡር ዕንቁ ይልቅ ይወደዳል፥ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።


ለአባቶቻቸው፦ እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ።


ስለዚህም የእስራኤል አምላክ ጌታን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።


እነሆም፥ ለጌታ በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያ በላያችሁ ተሹመዋል፤ ሌዋውያኑም ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ይሆናሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፥ ጌታም መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።”


“ጽኑ፥ አይዞአችሁ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና የአሦርን ንጉሥና ከእርሱ ጋር ያለውን ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ድምፅሽን ከልቅሶ ዓይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ የሚከፈልሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ፥ ይላል ጌታ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናንት፥ መቅደሱ እንዲሠራ የሠራዊት ጌታ ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ፥ እጃችሁን አበርቱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች