2 ዜና መዋዕል 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ኢዮርብዓም ግን ድብቅ ጦር በስተ ኋላቸው አዞረ፤ እነርሱ በይሁዳ ፊት ለፊት ሆነው ድብቅ ጦሩ ግን በስተ ኋላቸው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሰራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሰራዊት በስተጀርባ እንዲያደፍጡ ላከ፤ የቀረውም ሰራዊት ከርሱ ጋራ የይሁዳን ሰራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙ አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሠራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሠራዊት በስተጀርባ በማድፈጥ፥ አደጋ እንዲጥሉ ሲልክ፥ የቀሩትን ደግሞ የይሁዳን ሠራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙአቸው አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ኢዮርብዓም ግን በስተኋላቸው ይመጣባቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞረባቸው፤ እነርሱ በይሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስተኋላቸው ከበባቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ኢዮርብዓም ግን ድብቅ ጦር በስተኋላቸው አዞረ፤ እነርሱ በይሁዳ ፊት ሆነው ድብቅ ጦሩ በስተ ኋላቸው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |