2 ዜና መዋዕል 11:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ኢዮርብዓምና ልጆቹ ሌዋውያኑን ከእግዚአብሔር የክህነት አገልግሎት ስላባረሯቸው ሌዋውያኑ ማሰማሪያ ቦታቸውንና ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓምና በእርሱ እግር የተተኩት ዘሮቹ ሌዋውያንን የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ስላልፈቀዱላቸው ሌዋውያን ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የግጦሽ ቦታዎቻቸውንና የቀረውንም ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የእግዚአብሔርም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰምሪያቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የእግዚአብሔርም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማርያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ምዕራፉን ተመልከት |