Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲሁም ዲያቆናት መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ቃላቸውን የማያጥፉ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለገንዘብ የማይስገበገቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዲያቆናትም እንደዚሁ የተከበሩ፣ ቃላቸውን የማይለዋውጡ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጐመጁ፣ ያለ አግባብ የሚገኝ ጥቅምንም የማያሳድዱ ሰዎች መሆን ይገባቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲሁም ዲያቆናት የተከበሩና በቃላቸው የሚጸኑ፥ ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፥ ለገንዘብ የማይስገበገቡ መሆን አለባቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 3:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤


እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤


ስለ ሆድህና በተደጋጋሚ ስለሚያጠቃህ በሽታ ስትል ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ከእንግዲህ ውሃ ብቻ አትጠጣ።


የማይሰክር፥ የማይቆጣ ነገር ግን ታጋሽ የሆነ፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ገንዘብን የማያፈቅር፥


“እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤


ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም።


ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥


ዲያቆናት ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመልካም እያስተዳደሩ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።


ካህናቱ ሁሉ ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሚገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ አይጠጡ።


ኤዶማዊው ዶይቅ መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል ብሎ በነገረው ጊዜ፥


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥ መንገዴን በፊትህ አቅና።


ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤


“ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም አታለዋል፤” “የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤”


አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።


እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች