Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ ልከኛ፣ ራሱን የሚገዛ፣ በሥርዐት የሚኖር፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማስተማር የሚችል፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 3:2
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌታም ባርያ ጠበኛ መሆን አይገባውም፤ ይልቁንስ ለሰው ሁሉ ገር፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥


ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


መበለቲቱ ከስልሳ ዓመት በታች ያልሆነች፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች በመዝገብ ትጻፍ፤


ያለ ማጉረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነትን ተቀባበሉ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።


እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች በዚህ ሳቢያ ሳያውቁ መላእክትን በእንግድነት ተቀብለዋል።


ሽማግሌዎች በመጠን የሚኖሩ፥ ክብራቸውን የሚጠብቁ፥ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም በእውነት የጸኑ እንዲሆኑ ምከራቸው፤


በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤


የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል፤ እንግዲህ መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ።


የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤


እነርሱም መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን ላወቁት፥ ከምስጋና ጋር እግዚአብሔር የፈጠረውን ምግብ ከመቀበል እንዲቆጠቡ ያዝዛሉ።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር።


ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።


ከአሴር ወገንም የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ በዕድሜዋም በጣም የገፋች ነበረች፤ እርሷም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤


እንዲሁም ዲያቆናት መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ቃላቸውን የማያጥፉ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለገንዘብ የማይስገበገቡ፥


ዲያቆናት ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመልካም እያስተዳደሩ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።


እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች