Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “ኀጢአተኞችን ለማዳን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋነኛው እኔ ነኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ሁሉ የባስሁ ኃጢአተኛ እኔ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ኀጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 1:15
41 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም፤” አላቸው።


የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና፤” አለው።


ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና፤ ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም።


ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑበትን ሥልጣን ሰጣቸው፤


ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”


ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


ይሁንና ከዚህ ቀደም ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም የነበርኩ ብሆንም እንኳ ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ፤


የሰው ልጅም ሊያገለግል፥ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ፥ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ እንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አሳድጃለሁ፤


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።


ሂዱና ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤’ የሚለው ምን እንደሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤”


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


ለዚህም ነው፥ እነርሱን ሊያማልድ ዘወትር ይኖራልና፥ በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።


ይህ ቃል የታመነና ሁሉ ሰው ሊቀበለው የሚገባ ነው፤


ገና ደካሞች ሳለን፥ በትክክለኛው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና።


ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ጀምሮ ኃጢአትን ይሠራል። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።


“ማንም ኤጲስ ቆጶስነት ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል፤” የሚለው ቃል የታመነ ነው።


ከቅዱሳን ሁሉ ያነስኩ ብሆንም፥ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እንድሰብክ፥ ይህ ጸጋ ለኔ ተሰጠ፤


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባርያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤


እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው፦ “ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤


ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”


በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። እኔንም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።


ምስክርነቱ ይህ ነው፦ እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት ሰጠን፥ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው።


ይህን በምታደርግበት ጊዜ ግን እምነትንና በጎ ኅሊናን ይዘህ ይሁን፤ አንዳንዶች ሕሊናን ወደ ጎን በማድረግ፥ በእምነት ረገድ በማዕበል እንደተሰባበረች መርከብ ጠፍተዋል፤


“ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና “እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ሐዋርያትና በይሁዳም የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ተቀበሉ ሰሙ።


ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፥ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።”


ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ይህስ ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል፤” ብለው እርስ በርሳቸው አጉረመረሙ።


ይህም ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ ነው።


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለማዳን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች