1 ሳሙኤል 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ብንያማዊ ሰው ነበረ፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጸሮር ልጅ፥ የበኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፊሐ ልጅ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ቂስ የተባለ አንድ ታዋቂ ብንያማዊ ሰው ነበረ፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፣ የጽሮር ልጅ፣ የብኮራት ልጅ፣ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከብንያም ነገድ ቂስ ተብሎ የሚጠራ ታዋቂነት ያለው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጸሮር የልጅ ልጅ ሲሆን ከአፊሐ ጐሣ ወገን የበኮራት ቤተሰብ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ብንያማዊ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |