1 ሳሙኤል 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያን ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋራ ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያ ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት መልሳችሁ ለመላክ ብትፈልጉ፥ ስለ በደላችሁ የሚከፈል ስጦታ አብራችሁ መላክ ይገባችኋል፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት ያለ ምንም ስጦታ ተመልሶ መሄድ የለበትም፤ በዚህም ዐይነት እናንተ ከሕመማችሁ ትፈወሳላችሁ፤ እርሱ እናንተን በብርቱ የቀጣበትንም ምክንያት ልታውቁ ትችላላችሁ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳኑን ታቦት ብትሰድዱአት ስለ አሳዘናችሁአት የበደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶዋን አትስደዱአት፤ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፤ ስርየትም ይደረግላችኋል፤ አለዚያ ግን የእግዚአብሔር እጅ ከእናንተ አይርቅም” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እነርሱም፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ብትሰድዱ የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፥ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፥ እጁም ከእናንተ አለመራቁ ስለ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አሉ። ምዕራፉን ተመልከት |