1 ሳሙኤል 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የጌታ እጅ በአሸዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መቅሠፍት መታቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መታቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እግዚአብሔርም የአሽዶድን ሕዝብ በብርቱ አስጨነቃቸው፤ እነርሱንና በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝብ ሁሉ በእባጭ መቅሠፍት ቀጣቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው። ምዕራፉን ተመልከት |