1 ሳሙኤል 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ጌታም በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም ጌታ በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እግዚአብሔር በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም እግዚአብሔር ቃል አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እግዚአብሔርም በሴሎ መገለጡን ቀጠለ፤ እዚያም በቃሉ ለሳሙኤል ተገለጠለት። የሳሙኤልም ቃል በመላው እስራኤል ተደማጭነትን አገኘ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ። እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይገለጥለት ነበርና። ሳሙኤልም ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክፋት ጸንተው ኖሩ፤ መንገዳቸውም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፥ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር። የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ። ምዕራፉን ተመልከት |