Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልጆቹ በእኔ ላይ የንቀት ተግባር ሲፈጽሙ እርሱ ስላልገሠጻቸው ቤተሰቡን ለዘለዓለም እቀጣለሁ ብዬ ነግሬዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልጆቹ የእርግማን ነገር እንዳደረጉ አውቆ አልከለከላቸውምና ስለ ኃጢአቱ በቤቱ ለዘላለም እንድፈርድ አስታውቄዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባቱም በሕይወቱ ሳለ፦ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ ከቶ ተቆጥቶት አያውቅም ነበር። ደግሞም መልከ መልካም ነበር፤ የተወለደውም ከአቤሴሎም በኋላ ነበር።


በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በደንብ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር ጌታ ራሱ ይቀጣሃል፤


አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”


ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።


በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።


አንተ ደግሞ ሌሎችን የረገምክበትን ጊዜ ልብህ ያውቃልና።


ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዱን ሰው እንደ መንገዱ እፈርዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ተመለሱ፥ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።


አሁን ፍጻሜ በአንቺ ላይ ነው፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እሰድዳለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ።


አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥


“አንድ ሰው፥ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥


ልባችን ቢወቅሰን እንኳ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።


የዔሊም ልጆች ለጌታ ክብር የማይሰጡ ስድ አደጎች ነበሩ።


በዚህም ዓይነት የጌታን መሥዋዕት ስላቃለሉ፥ የዔሊ ልጆች ኃጢአት በጌታ ፊት ከፍተኛ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች