Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ነግቶ የወይን ጠጁ ስካር ካለፈለት በኋላ የሆነውን ሁሉ ስትነግረው ልቡ ቀጥ አለ፤ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በነጋታውም የወይን ጠጅ ስካሩ ካለፈለት በኋላ ሚስቱ የሆነውን ሁሉ ለናባል ስትነግረው ልቡ ቀጥ አለ፤ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 በማግስቱም ስካሩ ከበረደለት በኋላ ሁሉንም ነገር አስረዳችው፤ ልቡም በድንጋጤ ስለ ተመታ እንደ ድንጋይ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በነ​ጋ​ውም የወ​ይኑ ስካር ከና​ባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው፤ ልቡም በው​ስጡ ሞተ፤ እንደ ድን​ጋ​ይም ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በነጋውም የጠጁ ስካር ከናባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገረችው፥ ልቡም በውስጡ ሞተ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:37
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ይመታሃል።


ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ በሕይወት ባስቀር እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያድርግበት፥ ከዚህም የከፋ ይጨምርበት!”


ጉዳት እንዳላደርስብሽ የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው ጌታን! እንዲህ በቶሎ መጥተሽ ባታገኚኝ ኖሮ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ለናባል አንድ ወንድ እንኳ ባልተረፈ ነበር።”


አቢጌልም ወደ ናባል በተመለሰች ጊዜ፥ እነሆ፤ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ትልቅ ግብዣ አድርጎ አገኘችው፤ ክፉኛም ሰክሮ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እስኪ ነጋ ድረስ ምንም አልነገረችውም።


ዐሥር ቀን ያህል ካለፈ በኋላ፥ ጌታ ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች