Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 25:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታም በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ባደረገልህና በእስራኤልም ላይ በሚያነግሥህ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እግዚአብሔር ለጌታዬ በሰጠው ተስፋ መሠረት በጎውን ነገር ሁሉ ባደረገለትና በእስራኤልም ላይ ባነገሠው ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ባደረገልህና በእስራኤልም ላይ በሚያነግሥህ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቸር​ነት ሁሉ ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ አድ​ርጎ ይሾ​ም​ሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔርም ለጌታዬ የተናገረውን ቸርነት ሁሉ ባደረገልህ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ አለቃ አድርጎ ባስነሣህ ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 25:30
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁን ግን መንግሥትህ አይጸናም፤ ጌታ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው አግኝቶአል፤ አንተ የጌታን ትእዛዝ ባለመጠበቅህም፥ እርሱን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መርጦታል።”


በዚያ ጊዜ ለታማኞችህ በራእይ ተናገርህ፥ እንዲህም አልህ፦ ረድኤቴን በኃያል ላይ አኖርሁ፥ ከሕዝቤ የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ።


እርሱም፥ “አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል እጁን በአንተ ላይ አያሳርፍም፤ በእስራኤል ላይ ትነግሣለህ፤ እኔም ካንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ፤ ይህንም አባቴ ሳኦል እንኳ ያውቀዋል” አለው።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ጌታዬ የምታዝንበት ምክንያት ወይም የኅሊና ጸጸት አይኖርብህም፤ ምክንያቱም በከንቱ ያፈሰስከው ደም ወይም በገዛ እጅህ የወሰድከው በቀል የለምና። ስለዚህ ጌታ ለጌታዬ በጎ ነገር ባደረገልህ ጊዜም፥ እኔንም አገልጋይህን አስበኝ።”


እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


እነሆ፤ አንተ በእርግጥ እንደምትነግሥና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደምትጸና ዐውቃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች