Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 2:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከአንተ ዘሮች መካከል በሕይወት የሚተርፍ ሁሉ ወደዚያ ካህን ዘንድ እየሄደ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ከእርሱ ገንዘብና ምግብ ይለምናል፤ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘትም ሲል ካህናትን በረዳትነት ማገልገል እንዲፈቀድለት ይለምናል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፥ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እበላ ዘንድ ከካህናት ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ አንድ ብር አንድ እንጀራም ይለምናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 2:36
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ሰሎሞን አብያታርን የጌታ ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዓይነት ጌታ በሴሎ ስለ ካህኑ ዔሊና ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።


እነዚያም ካህናት በቤተ መቅደስ ከማገልገል ታገዱ፤ ይሁን እንጂ ለጓደኞቻቸው ካህናት ይሰጥ የነበረውን እርሾ ያልነካው ኅብስት እንዲመገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር።


ኃጢአተኞች በደጎች ፊት ይጐነበሳሉ፥ ኀጥኣንም በጻድቃን በር።


“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።


ሚካም፥ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።


የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤም የሚያደርግ ይሆናል፤ እኔም የጸና ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑንም ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።


ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች