1 ሳሙኤል 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ “ለጌታ ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት ጌታ ዘር ይስጥህ” ብሎ ባረካቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ዔሊም፣ “በጸሎት ባገኘችውና ለእግዚአብሔር በሰጠችው ልጅ ምትክ እግዚአብሔር ከዚህችው ሴት ዘር ይስጥህ” እያለ ሕልቃናንና ሚስቱን ይመርቃቸው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ዔሊም ሕልቃናን ከሚስቱ ከሐና ጋር በሚመርቅበት ጊዜ፥ ሕልቃናን “ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጋችሁ በሰጣችሁት በዚህ ልጅ ፈንታ ከዚህቹ ሴት ሌሎችን ልጆች ይስጥህ!” ይለው ነበር። ከዚያን በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን ባረካቸው፥ “ለእግዚአብሔር ስለ አገባኸው ስጦታ ፈንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር ዘር ይስጥህ” አለው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ገቡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ ለእግዚአብሔር ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር ዘር ይስጥህ ብሎ ባረካቸው፥ እነርሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከት |