Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሳሙኤልም ባገኘው ጊዜ ሳኦል፥ “ጌታ ይባርክህ! የጌታን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሳሙኤል ባገኘው ጊዜ ሳኦል፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሳሙኤል ወደ ሳኦል ሄደ፤ ሳኦልም “ሳሙኤል ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሳሙ​ኤ​ልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “አንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ክህ ሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ፈጽ​ሜ​አ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፥ ሳኦልም፦ አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 15:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቦዔዝም አላት፦ “ልጄ ሆይ፥ በጌታ የተባረክሽ ሁኚ፥ ባለ ጠጋ ይሁን ወይም ድሀ፥ ወጣቶችን መርጠሽ መሄድ አልፈለግሽምና ከፊተኛው ይልቅ አሁን ባደረግሽው ታማኝነትን አድርገሻል።


እናቱን፥ “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፥ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፥ “ልጄ፤ ጌታ ይባርክህ” አለችው።


ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፥ ቀማኛና ዐመፀኛ አመንዝራም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤


እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፤’ በሉ።”


ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።


በትዕቢት ከፍ ከፍ ያሉ ዐይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ አጋግን፥ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፥ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፥ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።


እንዲህም ሲል ባረከውም፦ አብራም ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፥ ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ፥


አዳምም፦ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኽኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።


ሌላ ያመስግንህ እንጂ ከአንተ አፍ አይውጣ፥ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይሁን።


ልክ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንዳበቃ፥ ወዲያውኑ ሳሙኤል ደረሰ፤ እርሱም ሊቀበለው ወጣ።


ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለ፤ “የጌታን ቃል ታዝዣለሁ፤ ጌታ በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።


ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢጌል እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ዳዊት ሰላምታውን እንዲያቀርቡለት ከምድረበዳ ወደ ጌታችን መልእክተኞች ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን በስድብ አዋረዳቸው።


እርሱም ወደ ያቤሽ ገለዓድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፥ “በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር በጎነት በማሳየታችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤


ሳኦል እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለእኔ ስለ ተቆረቆራችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች