Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ሳኦልም፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ሳኦልም፣ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሳኦልም፦ በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ አለ። ዮናታንም ተያዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:42
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች።


እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።


የቤቱንም ሰዎች አንድ በአንድ አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የዛራ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የከርሚ ልጅ አካን ተለየ።


ሳኦል፥ “ትክክለኛውን መልስ ስጠኝ” ሲል ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ዕጣው በሳኦልና በዮናታን ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም ነጻ ሆነ።


ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች