Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፥ መጥረቢያቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፣ ጠገራቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እንዲሁም እስራኤላውያን ማረሻቸውንና ዶማቸውን ለማሾል፥ መጥረቢያቸውንና ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን መውረድ ነበረባቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ማረ​ሻ​ው​ንና ማጭ​ዱን፥ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንና መቈ​ፈ​ሪ​ያ​ውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ርዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስራኤልም ሁሉ የማረሻውን ጫፍና ማጭዱን መጥረቢያውንና መቆፈሪያውን ይስል ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:20
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የምናሴንና የኤፍሬምንም የስምዖንና የንፍታሌምንም ከተሞች፥ በዙሪያቸውም ያለውን ቦታ እንዲሁ አነጻ።


ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን እንዲሁ።


የሚያንጸባርቅ ሰይፌን ከሳልኩ፥ እጄም ለፍርድ ካነሳችው፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እመልሳለሁ።


በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው።


ማረሻና ዶማ ለማሾል የሚከፈለው ዋጋ ሁለት ሦስተኛ ሰቅል ሲሆን፥ መጥረቢያ ለማሳል፥ መውጊያ ለማበጀት ደግሞ ዋጋው አንድ ሦስተኛ ሰቅል ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች