Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ ጌታ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ዛሬ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ባጸናልህ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ጠብቀኸው ቢሆን ኖሮ፣ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሳሙኤልም ሲመልስለት እንዲህ አለው፤ “ይህ የሞኝነት አሠራር ነው፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ አልፈጸምክም፤ ትእዛዙን ብትፈጽም ኖሮ አንተና ዘሮችህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም እንድትነግሡ ዛሬ መንግሥትህን ባጸናልህ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በድ​ለ​ኻል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛ​ዙን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ን​ቶ​ልህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሳሙኤልም ሳኦልን፦ አላበጀህም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፥ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጽንቶልህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:13
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቼን እንድስም ስለምን አልፈቀድህልኝም? ይህንም በስንፍና አደረግህ።


ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።


ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!


ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።


እንዲሁ ሳኦል በጌታ ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የጌታንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥


ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”


ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።


ማንም ሰው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኰንኖቹን፦ ክፉዎች ናችሁ ይላልን?


ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል።


ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፦ “የሠራዊትን ጌታ ቃል ስማ።


በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ድምፄንም ባይሰማ፥ እኔ ላደርግለት ስለ ተናገርሁት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።


ሐና ግን አልሄደችም፤ ምክንያቱም ለባሏ፥ “ሕፃኑ ጡት እንደተወ፥ በጌታ ፊት ቀርቦ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም በዚያ እንዲኖር፥ አመጣዋለሁ” ብላው ነበርና ነው።


ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የጌታን ርዳታ አልለመንሁም፥ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


ሳሙኤልም፦ “ጌታ ለቃሉ በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፥ ጌታ፥ በሚቃጠል ቁርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


ሳኦልም፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለከበረች ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ ይሄው፥ የሞኝ ሥራ ሠራሁ፤ አብዝቼም ተሳሳትኩ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች