1 ሳሙኤል 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ወደ ጌታ ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ ይህ በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ታበሳጫት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ይህም በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ ሐና ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ታበሳጫት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ይህም ሳይቋረጥ በየዓመቱ የሚደጋገም ነገር ነበር፤ ይኸውም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሄዱ ቊጥር ሐና እያለቀሰች ምግብ ለመብላት እምቢ እስከምትል ድረስ ጵኒና በብርቱ ታበሳጫት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በየዓመቱም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚወጣበት ጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ እርስዋም ትበሳጭና ታለቅስ ነበር። እህልም አትበላም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በየዓመቱም እንዲህ ባደረገ ጊዜ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር በምትወጣበት ጊዜ ታበሳጫት ነበር፥ ሐናም ታለቅስ ነበር፥ አንዳችም አትቀምስም ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |