1 ሳሙኤል 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም አንዲቱ ሐና፥ ሁለተኛዪቱም ጵኒና ነበር። ጵኒና ልጆች ነበሯት፤ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እርሱም አንዲቱ ሐና፣ ሌላዪቱ ፍናና የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍናና ልጆች ሲኖሯት፣ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ሕልቃናም ሐናና ፍኒና ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍኒና ልጆች ነበሩአት፤ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና፥ የሁለተኛዪቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፤ ለሐና ግን ልጆች አልነበሩአትም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ሁለትም ሚስቶች ነበሩት የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፥ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፥ ለሐና ግን ልጅ አልነበራትም። ምዕራፉን ተመልከት |