3 እነሆ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችኋልና።
3 ጌታ መልካም መሆኑን ቀምሳችኋልና።
3 ልትመኙ የምትችሉትም “ጌታ ለጋስ መሆኑን ዐውቃችሁ እንደ ሆነ ነው።”
የጌታ መልአክ ጌታን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
በጎነቱ በውበቱም እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጎልማሶችን፥ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅቱን ያሳምራል።
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥ በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።
ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥