Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 8:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም ሰሎሞን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉም በተገኙበት ተነሥቶ በጌታ መሠዊያ ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ሰሎሞን መላው የእስራኤል ጉባኤ ባለበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሕዝቡ ፊት ተነሥቶ በመሠዊያው ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ቆሞ እጆ​ቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎሞን በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 8:22
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።


እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።


በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ ልብሴና ካባዬ እንደተቀደደ ከተዋረድኩበት ተነሣሁ፥ በጉልበቴም ተንበርክኬ ወደ ጌታ አምላኬ እጄን ዘረጋሁ፤


“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥


ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።


ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።


ሕዝቡ ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ይሰግድ ነበር።


ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።


ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፥ እጁንም ወደ ጌታ ዘረጋ፤ ነጎድጓዱም በረዶውም ቆመ፥ ዝናቡም ወደ ምድር አልዘነበም።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች