Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “እነሆ ጌታ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ ቦታ ተተክቼ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀመጥኩ፤ ጌታም ቃል እንደገባው፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ለስሙ ቤት ሠራሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጽሟል፤ እኔም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ቤተ መቅደስንም ሠርቼአለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተነ​ሣሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል አጸና፤ እግዚአብሔርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፤ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፤ ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 8:20
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕድሜህን ጨርሰህ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ፥ በእግርህ እንዲተካ ከአብራክህ የተከፈለ ዘር አስነሣልሃለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።


ንጉሡም ደግሞ፦ ‘ዓይኔ እያየ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይመስገን!’ አለ።”


እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦


ልቡም በፊትህ ታማኝ ሆኖ አገኘኸው፥ የከነዓናዊውን፥ የኬጢያዊው፥ የአሞራዊውን፥ የፌርዛዊውን፥ የኢያቡሳዊውንና የጌርጌሳዊውን ምድር ለዘሩ ልትሰጥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፥ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን ፈጸምህ።”


ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፥ ስለ ጽኑ ፍቅርሀና ስለ ታማኝነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህንና ቃልህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።


ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።


ነገር ግን እኔ ጌታ የምናገረውን ቃል እናገራለሁ፥ ይፈጸማልም፥ ደግሞም አይዘገይም፥ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመዋለሁም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


መንፈሴን በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁ አስቀምጣችኋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደ ተናገርሁ፥ እንዳደረግሁትም ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ።


ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን እንደማልህላቸው እውነትን ለያዕቆብ፥ ርኅራኄን ለአብርሃም ታደርጋለህ።


ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት።


የሰጠውንም ተስፋ እንደሚፈጽም ጽኑ እምነት ነበረው።


በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽመው በዚህ እርግጠኛ ሆኛለሁ፤


ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች