Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 7:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን እና ጐድጓዳ ሳሕኖችን። ኪራም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ ኪራም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሠራ። በን​ጉሡ ቤትና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም አርባ ስም​ንት አዕ​ማድ ነበሩ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ የሠ​ራ​ቸው ዕቃ​ዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም አደረገ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራው ይህ ዕቃ ሁሉ የጋለ ናስ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 7:45
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችን፥ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደሱ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ።


ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም-አቢ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለጌታ ቤት ከተሰነገለ ናስ ሠራ።


አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ።


የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ፥ ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፥ ሜንጦቹን፥ ማንደጃዎቹን ሠራ፤ ዕቃዎቹን በሙሉ ከነሐስ ሠራ።


የሸክላ ድስቶችንና መጫሪያዎችንም፥ መኰስተሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሙዳዮችና የሚገለገሉባቸውንም የናስ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ።


ሙሴም አሮንንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉ፤ ከዚህም ጋር ‘አሮንና ልጆቹ ይበሉታል’ ብዬ እንዳዘዝሁ የቅድስናው መሥዋዕት እንጀራ ከሚቀመጥበት መሶብ ውስጥ ያለውን እንጀራ በዚያ ትበሉታላችሁ።


በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች