1 ነገሥት 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የገንዳው አፍ ውጫዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ፥ ቅርጾች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ከገንዳው ከንፈር በታችም፣ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ እንደ ቅል ያሉ ዐሥር ቅርጾች ዙሪያውን በሁለት ረድፍ ከብበውታል፤ እነዚህም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ተሠርተው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የገንዳው አፍ ውጫዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ፥ ቅርጾች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ከከንፈሩም በታች ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድ ክንድም ዐሥር ጕብጕቦች አዞረበት፤ ከንፈሮቹም እንደ ጽዋ ከንፈር ነበሩ። በውስጡም አበቦች በቅለውበት ነበር። ውፍረቱም ስንዝር ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ከከንፈሩም በታች ለአንድ ክንድ ዐሥር ለአንድ ክንድም ዐሥር ጉብጉቦች አዞረበት፤ እርሱም በቀለጠ ጊዜ ጉብጉቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |