1 ነገሥት 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ሰሎሞንም ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚሰጡ በእስራኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞችን ሾመ። ከዓመቱ ውስጥ እያንዳንዱን ወር እያንዳንዳቸው ይቀልቡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ለንጉሡና ለቤተ ሰቡም ቀለብ የሚሰጡ በእስራኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞች ለሰሎሞን ነበሩት። ከዓመቱ ውስጥ አንዱን ወር እያንዳንዳቸው ይቀልቡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |