Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሌላዪቱም ሴት፣ “ነገሩ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤ የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለውም የእኔ ነው” አለች። የመጀመሪያዋ ሴት ግን አጠንክራ፣ “አይደለም! የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው” አለች፤ በዚህ ሁኔታም በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዐይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት፥ “አይ​ደ​ለም ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እን​ዲ​ሁም በን​ጉሡ ፊት ይነ​ጋ​ገሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሁለተኛይቱም ሴት “ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤” አለች። ይህችም “የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው፤” አለች፤ እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 3:22
2 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ የሞተ ሆኖ አገኘሁት፤ ትኲር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች