Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሚክያስም፣ “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ፤ ቀጥሎም፣ “እናንተ ሰዎች ሁላችሁ ስሙኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሚክያስም “በደኅና ብትመለስ እግዚአብሔር በእኔ የተናገረ አይደለም፤” አለ። ደግሞም “አሕዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 22:28
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቦች ሆይ! ሁላችሁም ስሙ፤ ምድርና ሞላዋ ታድምጥ፤ ጌታ በቅዱስ መቅደሱ ሆኖ፥ ጌታ አምላክ በእናንተ ላይ ይመስክርባችሁ።


እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ ሰው እንደሚሞተው ቢሞቱ፥ ወይም ሰው ሁሉ እንደሚቀበለው የዕጣ ክፍሉ የሚቀበሉ ቢሆን እኔን ጌታ አልላከኝም።


“ታዲያ ዳዊት ራሱ ጌታ፥ ካለው፤ እንዴት ተመልሶ ልጁ ይሆናል?”። ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰማው ነበር።


የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤


የባርያዬን ቃል አጸናለሁ፤ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ።


ሚክያስም እንዲህ አለ፦ “በደህና የተመለስህ እንደሆነ ጌታ በእኔ አልተናረም።” ዳግመኛም እርሱ፦ “እናንተ ሕዝቦች ሆይ! ሁላችሁም ስሙኝ!” አለ።


ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።


ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።


ነገር ግን በጆሮህና በሕዝብ ሁሉ ጆሮ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች