Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 20:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ፥ ነቢዩ ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ጥሬ ብር መቀጫ ትከፍላለህ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ንጉሡ በዚያ በሚያልፍበትም ጊዜ፣ ነቢዩ ጠርቶት እንዲህ አለው፤ “እኔ አገልጋይህ በተፋፋመው ጦርነት መካከል ገብቼ ሳለሁ፣ አንድ ሰው ምርኮኛ ይዞ መጥቶ ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ በገመዱ ትገባለህ ወይም አንድ መክሊት ብር ትከፍላለህ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ፥ ነቢዩ ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ጥሬ ብር መቀጫ ትከፍላለህ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 20:39
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወዲያውም እርሱና ኢዮናዳብ ለበዓል የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም ልዩ ልዩ መሥዋዕት ለማቅረብ ገቡ፤ ከዚህም ቀደም ብሎ ኢዩ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሰማኒያ ወታደሮች በማሰለፍ “እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንድትገድሉ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ እንዲያመልጥ የሚያደርግ ማንም ሰው ቢኖር በዚያ ሰው ምትክ እርሱ ራሱ ይገደላል!” ሲል መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር።


ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።


እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥ ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።


በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥


ሀብት ወደ ስድብ አስቶ እንዳይወስድህ፥ ትልቅ ጉቦም ከመስመር እንዳያስወጣህ።


ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል።”


ካሳ እንዲከፍል ቢወሰንበት ግን፥ የነፍሱን ካሳ የወሰኑበትን ያህል ይስጥ።


ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያና ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ።” ንጉሡም “በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል” አለው።


የጌታን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፥ ደም ከማፍሰስም ሰይፉን የሚከለክል ርጉም ይሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች