1 ነገሥት 2:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 እርሱም ወደ ጌታ ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን “ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። ኢዮአብ ግን “አልወጣም! እዚሁ እሞታለሁ!” አለ። በናያም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ስለዚህም በናያስ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ገብቶ ኢዮአብን፣ “ንጉሡ፣ ‘ከዚህ ውጣ’ ይልሃል” አለው። እርሱ ግን “አልወጣም፣ እዚሁ እሞታለሁ” አለው። በናያስም፣ “ኢዮአብ የሰጠኝ መልስ ይህ ነው” በማለት ለንጉሡ ተናገረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 እርሱም ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን “ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። ኢዮአብ ግን “አልወጣም! እዚሁ እሞታለሁ!” አለ። በናያም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 የዮዳሄ ልጅ በንያስም ወደ ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይልሃል” አለው፤ ኢዮአብም፥ “በዚህ እሞታለሁ እንጂ አልወጣም” አለ። የዮዳሄ ልጅ በንያስም፦ ተመልሶ “ኢዮአብ የተናገረው ቃል፥ የመለሰልኝም እንዲህ ነው” ብሎ ለንጉሡ ነገረው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 በናያስም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን መጥቶ “ንጉሡ ‘ውጣ’ ይልሃል፤” አለው፤ እርሱም “በዚህ እሞታለሁ እንጂ አልወጣም፤” አለ። በናያስም “ኢዮአብ የተናገረው ቃል የመለሰልኝም እንዲህ ነው፤” ብሎ ወደ ንጉሡ ወሬ አመጣ። ምዕራፉን ተመልከት |