1 ነገሥት 18:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 “በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ “አሁንም ጨምሩበት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ እርሱም “አሁንም እንደገና አንድ ጊዜ ጨምሩ!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ደግሞም፣ “እንደ ገና ጨምሩበት” አላቸው፤ እነርሱም ጨመሩበት። “ሦስተኛም ጨምሩበት” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ለሦስተኛ ጊዜ ጨመሩበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 “በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ “አሁንም ጨምሩበት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ እርሱም “አሁንም እንደገና አንድ ጊዜ ጨምሩ!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 “አራት ጋን ውኃ አምጡልኝ፤ በሚቃጠለው መሥዋዕትና በእንጨቱ ላይም አፍስሱ” አለ፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ። ደግሞም፥ “ድገሙ” አለ፤ እነርሱም ደገሙ። እርሱም፥ “ሦስተኛ አድርጉ” አለ፤ ሦስተኛም አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 ደግሞም “ድገሙ” አለ፤ እነርሱም ደገሙ። እርሱም “ሦስተኛ አድርጉ፤” አለ፤ ሦስተኛም አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከት |