Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ስለዚህም ኤልያስ ራሱን በአክዓብ ፊት ለመግለጥ ሄደ። በዚህ ጊዜ ራብ በሰማርያ ክፉኛ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኤል​ያ​ስም ለአ​ክ​ዓብ ይገ​ለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ራብ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 18:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ስለምን ትፈራለህ?


ክፉ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፥ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ተማምኖ ይኖራል።


ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፥


ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥ የሚያስፈራኝ ማን ነው? ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?


ከበባውም የምግብን እጥረትና ብርቱ ራብ ከማስከተሉ የተነሣ፥ የአንድ አህያ ራስ ዋጋ እስከ ሰማኒያ ጥሬ ብር፥ ሁለት መቶ ግራም የሚያኽል የርግብ ኩስ ዋጋ ደግሞ አምስት ጥሬ ብር ማውጣት ጀመረ።


የእንጀራችሁንም በትር በሰበርሁ ጊዜ፥ ዐሥር ሴቶች እንጀራችሁን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው ዳግመኛ እንጀራችሁን ያመጡላችኋል፤ ትበላላችሁም ነገር ግን አትጠግቡም።


ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት ጌታ ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው።


ስለዚህም ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ ጌታን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነው።


ጉልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም የተትረፈረፈውን ምርትዋን አትሰጥም፥ የምድሪቱም ዛፎች ፍሬያቸውን አይሰጡም።


ስለዚህም እግዚአብሔር፥ ‘እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም! ከተኛህበት አልጋም አትነሣም! ብሎሃል’ በሉት።” ስለዚህ ኤልያስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤


በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሥጋ ምን ያደርገኛል?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች