1 ነገሥት 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ሴትዮዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና በአፍህ ያለው የጌታ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅሁ!” ስትል መለሰችለት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እርስዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት መናገሩን አሁን አረጋገጥኩ!” ስትል መለሰችለት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ሴቲቱም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ሴቲቱም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን አወቅሁ፤” አለችው። ምዕራፉን ተመልከት |