1 ነገሥት 17:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታ አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባሏ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርሷ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጇ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ከዚያም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ ልጇን እንዲሞት በማድረግ ተቀብላ በምታስተናግደኝ በዚህች መበለት ላይም መከራ ታመጣባታለህን?” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ኤልያስም፥ “እኔ በቤቷ ያደርሁ የዚች መበለት ምስክርዋ ጌታዬ ሆይ፥ ልጅዋን በመግደልህ ክፉ አድርገህባታልና ወዮልኝ!” ብሎ ጮኸ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ወደ እግዚአብሔርም “አቤቱ አምላኬ ሆይ! ልጅዋን በመግደልህ ይህችን ትቀልበኝ የነበረቺቱን ባልቴት እንዲህ ደግሞ አስጨነቅኻትን?” ብሎ ጮኸ። ምዕራፉን ተመልከት |