Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቁጣ አነሣሥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ከትቢያ አንሥቼ፣ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ አንተ ግን በኢዮርብዓም መንገድ ሄድህ፤ ሕዝቤ እስራኤል ኀጢአት እንዲሠራ፣ በኀጢአቱም ለቍጣ እንዲያነሣሣኝ አሳሳትኸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቊጣ አነሣሥቶአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “እኔ ከመ​ሬት አን​ሥቼ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ ግን በከ​ንቱ ጣዖ​ታ​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በአ​ሳ​ታ​ቸው በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄድህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔ ከመሬት አስነሥቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ አድርጌሃለሁ፤ አንተ ግን በኢዮርብዓም መንገድ ሄደሃል፤ በኀጢአታቸውም ያስቆጡኝ ዘንድ ሕዝቤን እስራኤልን አስተሃቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 16:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮርብዓም ኃጢአት ስለሠራና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለ መራ፥ ጌታ እስራኤልን ይተዋል።”


ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ።


ከእርሱም በፊት እንደነበረው እንደ አባቱ ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ።


ከእርሱም በፊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባዕሻ ራሱ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት ጌታን አሳዘነ።


ሙሴም አሮንን፦ “ይህንን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ?” አለው።


እኔን ለማስቆጣት፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ፥ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ፤ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቁርባን ያፈስሳሉ።


ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንድዋን እንኳ ችላ የሚል ሰዎችንም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ ነገር ግን የሚፈጽመው እንዲሁም የሚያስተምር ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።


ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤


ልጆቼ ሆይ፥ የጌታን ሕዝብ ኃጢአተኛ በማድረጋችሁ ስለ እናንተ የደረሰኝ ወሬ መልካም አይደለምና ይህ አይሆንም።


ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።


አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች