1 ነገሥት 16:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሆኖ ሰባት ቀን ብቻ ገዛ። በዚህ ጊዜ ሰራዊቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ የሆነችውን ገባቶንን ከብቦ ሰፍሮ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በቲርጻ አድርጎ በእስራኤል ላይ ሰባት ቀን ብቻ ነገሠ፤ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የጊበቶንን ከተማ ከበው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ዘጠነኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። የእስራኤል ሠራዊት ግን በፍልስጥኤም ሀገር በገባቶን ሰፍረው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በይሁዳ ንጉሥ በአሳ በኻያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። ሕዝቡም በፍልስጥኤም አገር የነበረው ገባቶንን ከብበው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |